● LiveWorld
በፊሊፒንስ በሬክተር ስኬል 7.8 በተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያስ ን የ32 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Brook News
Jun 8, 20261 min read
297
በፊሊፒንስ በደረሰ ሀይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ህንጻዎችን በማውደም እና በመላው እስያ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ አስገድዷል። የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ እንደገለጸው በሬክተር ስኬል 7.8 የተለካው የመሬት መንቀጥቀጡ በደቡባዊ ሚንዳናኦ ደሴት ላይ ሰኞ በሃገር ውስጥ ሰዓት አቆጣጠር 1፡40 ላይ ደርሷል ብሏል። በመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ ቢያንስ የ32 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ቢያንስ 129 ሰዎች መቁሰላቸውን ፖሊስ አረጋግጧል። የመሬት መንቀጥቀጡ በ37 ህንፃዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠባቸዉ ሀገራት መካከል ፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔዥያ እና ጃፓን ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
Filed under

