ሰሞኑን መነጋገሪ በነበረው የላሊበላው አጋጣሚ ቱሪስቱ (Davud Akhundzada)ሃሳብና ትዝብቱን አጋቷል::
By Ashenafi
Jul 27, 20261 min read
የ20 ዶላር አታላይ ግለሰብ መታሰርን አስመልክቶ ይህንን ብሏል "ግለሰቡ እንዲታሰር ፍላጎት የለኝም። በችግር እና በተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚፈጠር ድርጊት መሆኑን ስለምረዳ፣ ገጠመኜን ያቀረብኩት ሰውን ለመቅጣት ሳይሆን የጉዞ ልምዴን ለማካፈል ነው።"
"ላሊበላ በአውሮፓ ቢሆን ኖሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን ይስብ ነበር። ኢትዮጵያ ከዚህ ታላቅ የታሪክ ሀብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን የተሻለ ድርጅታዊ አሰራር፣ ሙያዊ ስልጠና፣ ግልጽነት እና ኢንቨስትመንት ያስፈልጋታል።" ያለ ሲሆን ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ያለውን ዋና ዋና ነጥቦች አጋርቷል ::
የ100 ዶላር የመግቢያ ክፍያ እና የአገልግሎት ክፍተት አለው ያለ ሲሆን ምክናየቱን እንዲ አጋርቷል "የ100 ዶላር ክፍያው ከመጠን ያለፈ ነው፤ ምክንያቱም ቦታው መሠረታዊ አገልግሎቶች፣ መሰረተ ልማቶች እና የደህንነት ከለላዎች ይጎድሉታል። ክፍያው ከፍ ያለ ከሆነ እንደ ፕሮፌሽናል አስጎብኚ፣ ካርታ፣ ንጹህ መፀዳጃ ፣ እና ግልጽነት ባላቸው አገልግሎቶች ሊደገፍ ይገባል።" የቱሪዝም አሰራር እና የጎብኚዎች ደህንነት በሚመለከት ደግሞ "የአካባቢው የቱሪዝም ሰራተኞች የተሻለ ስልጠና ያስፈልጋቸዋል። ጎብኚዎች "እንግሊዝኛ መለማመድ እፈልጋለሁ" በሚሉ እና በኋላ ላይ ገንዘብ በሚጠይቁ አታላይ አቀራረቦች ሰለባ እንዳይሆኑ እና ከወከባ ነፃ እንዲሆኑ የቱሪስት ፖሊስ ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል።"