የ ቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ማርያም (የጾመ ፍልሰታ) መልእክት
A
By Ashenafi
Aug 6, 20261 min read
134
ቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ማርያም (የጾመ ፍልሰታ) ወቅት ባስተላለፉት መልእክት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አጉልተው አሳስበዋል ምዕመናን የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ እንዲሁም ንስሐ በመግባትና ቅዱስ ቁርባን በመቀበል እንዲያሳልፉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።
አምላክን መውደድ በስሜት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ትእዛዛቱን በመጠበቅና በመተግበር የሚረጋገጥ ተግባራዊ ሕይወት እንደሆነ ገልጸዋል። ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ» ሲባል የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍልን ብቻ ሳይሆን በሕይወት ያሉትንም ሆነ ያለፉትን—መላውን የሰው ልጅ የሚያጠቃልል እንደሆነ አብራርተዋል።
ጾመ ማርያም አምላክ ቅዱሳንን እንድናከብር የሰጠንን ትእዛዝ መሠረት ያደረገ እንደሆነና ድንግል ማርያም ደግሞ ከፍጥረታት ሁሉ በላይ የሆነ ልዩ ክብርና ልዕልና ያላት የጌታ ማደሪያ መሆኗን ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ትልቅ ስጋት የሆነው አውዳሚ ጦርነት በእግዚአብሔር መልኮታዊ ጥበብ እንዲቆም ሁሉም በቅን ልቦና እና በትሕትና ሆኖ እንዲጸልይ አደራ ብለዋል።
Filed under