ራሺያን ለመምታት ኤለን መስክ ድጋፍ ተጠየቀ❗️
By Ashenafi
Sep 25, 20261 min read
🛰ራሺያን ለመምታት ኤለን መስክ ድጋፍ ተጠየቀ❗️
👉ዘ ጋርዲያን እና ሮይተርስ እንደዘገቡት፣ የፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ስተብ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከኢሎን ማስክ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት በሩሲያ ግዛት ውስጥም እንዲሠራ እና ዩክሬን እንድትጠቀምበት ጠይቀዋል።
👉🛰 በእጅጉ እየወደመች ያለችው ዩክሬን የአየር መከላከያ ሚሳይሎች እጥረት ስለገጠማት፣ ሩሲያ በግዛቷ ውስጥ ሆና ወደ ዩክሬን የሚሳይል ጥቃት የምታደርስባቸውን ተንቀሳቃሽ የባሊስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፊያዎች፤ የስታርሊንክን ሳተላይት እና ድሮኖችን በመጠቀም አድራሻቸውነሰ አውቃ ቀድማ ለመምታት አቅዳለች።
👉🛰 ፕሬዝዳንት ስተብ ይህ እርምጃ የሩሲያን ሚሳይሎች በመቀነስ የሰዎችን ሕይወት ይታደጋል የሚል እምነት አላቸው።
🛰 የኢሎን ማስክ ኩባንያ ስፔስ ኤክስ (SpaceX) ስታርሊንክን ለዩክሬን ወታደራዊ የግንኙነት እና የድሮን መቆጣጠሪያ ቢፈቅድም፣ አገልግሎቱ በሩሲያ ኦፊሴላዊ ግዛት ውስጥ እንዳይሠራ በጂኦ-ፌንሲንግ በሚባል ሲስተም ገድቦታል።
💵 ኤለን ማስክ ቀደም ሲልም ይፋዊ ውጊያው ከዩክሬን ወሰን ውጭ ወደ ሩሲያ ጥልቅ ግዛት እንዳይስፋፋ ስታርሊንክን ለጥቃት መጠቀምን ሲከለክል ቆይቷል።
🗡 ይህ ጥያቄ በጂኦፖለቲካው ዓለም ከፍተኛ ክርክር እና ስጋት ያስነሳ ጉዳይ ነው። የምዕራባውያን ቴክኖሎጂ እና ሳተላይቶች በሩሲያ ጥልቅ ግዛት ላይ ለሚደረጉ ወታደራዊ ጥቃቶች በቀጥታ ውሎ ማደራጀታቸው፣ በሩሲያ እና በኔቶ መካከል ያለውን ቀጥተኛ ግጭት ያባብሰዋል።
🇷🇺 ሩሲያ ይህንን እንደ ቀጥተኛ የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ስለምትቆጥረው፣ ሁኔታውን ወደ ባሰ አደገኛ ደረጃ (የኒውክሌር ስጋትን ጨምሮ) ሊያደርሰው ይችላል የሚል ስጋት አለ።
