● LiveAwards
ከፍተኛ ገንዘብ ተሸለመች💰
አትሌት ልቅና አምባው የ5000 ሜትር የአልቲሜት ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነች
A
By Ashenafi
Sep 14, 20261 min read
130
ከፍተኛ ገንዘብ ተሸለመች💰 አትሌት ልቅና አምባው የ5000 ሜትር የአልቲሜት ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነች
💎በአልቲሜት ሻምፒዮና የመጨረሻ ቀን በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር አትሌት ልቅና አምባው በአስደናቂ አቋም ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የሻምፒዮናው አሸናፊ ሆናለች።
💎አትሌት ልቅና 5000 ሜትሩን 14:30.36 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችላለች።
💎በውድድሩ የኢትዮጵያ አትሌቶች ጥሩ ውጤቶችን ያስመዘገቡ ሲሆን፣ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ 14:32.62 በሆነ ጊዜ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
💎አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ 14:32.76 በሆነ ጊዜ አራተኛ፣ አትሌት አለሺኝ ባወቀ 14:32.95 በሆነ ጊዜ አምስተኛ፣ እንዲሁም አትሌት ሰናይት ጌታቸው 14:38.65 በሆነ ጊዜ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
💎የአውስትራሊያ አትሌት ጄሲካ ሂል በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቃለች።
Filed under