በታሪካዊው ንግድ ባንክ (ክቡ) ሕንፃ ፊት ለፊት የሕንፃውን ውበት በእጅጉ የሚጎዳ የዘበኛ ቤት ቅጥያ ግንባታ እና ቅሬታ
A
By Ashenafi
Jul 25, 20261 min read
168
በታሪካዊው የአዲስ አበባ ንግድ ባንክ (ክቡ) ሕንፃ ፊት ለፊት የሕንፃውን ውበት በእጅጉ የሚጎዳ የዘበኛ ቤት ቅጥያ ግንባታ ተካሂዶ ነበር። በማህበራዊ ሚዲያ፣ በሙያተኞች እና በብዙኃን መገናኛ በተደረገው ተፅዕኖ የሕዝቡ ድምፅ ተሰምቶ ግንባታው ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ ተደርጓል። ጉዳዩ ትኩት እንዲያገኛል ሲጥር የቆየው ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ አፋጣኝ ምላሽ ለሰጡት ምስጋናው አቅርቧል ::
የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን፡ በኢ/ር ሕይወት ሳሙኤል የሚመራው ይህ ባለስልጣን ቅሬታውን ተቀብሎ ግንባታው እንዲፈርስ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወቱ ተመስግኗል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቁጥጥር ባለሥልጣኑ ጋር በመተባበር የሕዝብን ድምፅ ሰምቶ እርምጃ በመውሰዱ ምስጋና ቀርቦለታል። መገናኛ ብዙኃንና ሕዝብ፡ ድጋፍ የሰጡ፣ መረጃውን ያሰራጩ እና የተባበሩ አካላት በሙሉ ተመስግነዋል።