● LiveFootball
አፍሪካዊቷ ደሴት ሀገር ኬፕ ቨርዲ አስደናቂ ታሪክ በመስራት ጠንካራዋን ስፔን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አስቁማለች።
A
By Ashenafi
Jun 15, 20261 min read
380
አፍሪካዊቷ ደሴት ሀገር ኬፕ ቨርዲ አስደናቂ ታሪክ በመስራት ጠንካራዋን ስፔን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አስቁማለች። በአትላንታው መርሴዲስ-ቤንዝ ስታዲየም በተደረገው በዚህ የዓለም ዋንጫ የ ምድብ ጨዋታ ስፔን ሙሉ የጨዋታ የበላይነት የነበራት ቢሆንም የኬፕ ቨርዲው ግብ ጠባቂ ቮዚኛ በተለይም በፌራን ቶሬስ የተሰነዘሩ ሦስት ግልጽ የጎል ሙከራዎችን በማክሸፍ የሀገሩ ባለውለታ ሆኗል። በሁለተኛው አጋማሽ ላሚን ያማል እና ፔድሪ ቢገቡም የኬፕ ቨርዲን ጠንካራ መከላከል መስበር ሳይችሉ ቀርተዋል።
