በእግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ የእረፍት ሰዓት እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ታውቋል።
By Ashenafi
1d ago1 min read
በእግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ (ፋይናል) ጨዋታ የእረፍት ሰዓት (Half-time)፣ የአሜሪካው 'ሱፐር ቦውል' አይነት ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንት ለማስተናገድ ሲባል እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ታውቋል።
ይህ ታሪካዊ ክስተት እሑድ በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ስታዲየም በሚደረገው የ2026 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ይካሄዳል።
ይህንን የሙዚቃ ትዕይንት የኮልድፕሌይ (Coldplay) ባንድ መሪ ክሪስ ማርቲን ያዘጋጀው (curate ያደረገው) ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ እጅግ ዝነኛ የሆኑ አርቲስቶች በአንድ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ከተሳታፊዎቹ መካከል ጃስቲን ቢበር ማዶና ሻኪራ የደቡብ ኮሪያው ታዋቂ ባንድ ቢቲኤስ (BTS) የናይጄሪያው ድምፃዊ በርና ቦይ (Burna Boy) ታዋቂው የኦርኬስትራ መሪ ጉስታቮ ዱዳሜል (Gustavo Dudamel) ይገኙበታል።
በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ቦርድ (IFAB) ህግ መሰረት፥ የማንኛውም የእግር ኳስ ጨዋታ የዕረፍት ሰዓት ከ15 ደቂቃ መብለጥ የለበትም። ፊፋ (FIFA) ግን ይህንን ግዙፍ የሙዚቃ መድረክ ለመገንባት እና መልሶ ለማንሳት ጊዜ ስለሚያስፈልገው የራሱን ህግ በመጣስ እረፍቱን ለማራዘም ወስኗል። ይህ ውሳኔ ጨዋታው እንዲቋረጥና የተጫዋቾች አካላዊ ዝግጁነት (ሙቀት) ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚል በእግር ኳስ ተንታኞችና አፍቃሪያን ዘንድ መጠነኛ ቅሬታንና ክርክርን አስነስቷል።
Filed under

