TrendingAfrica
የኡጋንዳ ጦር አዛዥ በሀገሪቱ ካሉት ትላልቅ የሚዲያ ተቋማት መካከል ሁለቱን እንዲዘጉ ማዘዛቸውን ገለጹ።
A
By Ashenafi
Jun 28, 20261 min read
357
የኡጋንዳ ጦር አዛዥ በሀገሪቱ ካሉት ትላልቅ የሚዲያ ተቋማት መካከል ሁለቱን እንዲዘጉ ማዘዛቸውን ገለጹ።
ሙሆዚ ካይነሩጋባ እሁድ ዕለት እንደተናገሩት የሀገሪቱ ትልቁ ነጻ የዕለት ተዕለት ጋዜጣ የሆነው ዴይሊ ሞኒተር (Daily Monitor) እና አንደኛው ትልቅ የግል ስርጭት ጣቢያ የሆነው ኤንቲቪ ኡጋንዳ (NTV Uganda) እደዘጉና ያለ እሳቸው ፈቃድ እንደማይከፈቱ አስታውቀዋል።
በኡጋንዳ ውስጥ በነጻ ፕሬስ አላምንም!" ሲሉ የፕሬዝዳንቱ ልጅ የሆኑት ካይነሩጋባ በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
በተከታታይ ካወጧቸው መግለጫዎች በአንዱ ላይ "ከአሁን ጀምሮ ስለ ኡጋንዳ የሚወጡ ማናቸውም መጥፎ ታሪኮች በሙሉ በቢሮዬ መጽደቅ አለባቸው!" ካሉ በኋላ፣ ወደፊት በኡጋንዳ ያሉ ሁሉም ሚዲያዎች ህጎቹን እንደሚከተሉ አክለው ገልጸዋል። ዘገባው የ አልጀዚራ ነው
