● LivePolitics
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዳግመኛ ተመርጠዋል❗️
A
By Ashenafi
Oct 5, 20261 min read
46
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዳግመኛ ተመርጠዋል❗️
👉የገንዘብ ሚኒስትርን ጨምሮ አራት የካቢኔ አባላት እስካሁን ከሀላፊነት መነሳታቸው ታውቋል፡፡
ይህም በአዲሱ ካቢኔ እንደማይካተቱ ያሳያል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫቱ ሳኒ ፣ የመስኖና እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፡፡
እስካሁን ከሚኒስትርነት ሀላፊነታቸው ተነስተው በሌሎች የስራ ሀላፊነቶች ላይ የተሾሙ ናቸው፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አህመድ ሺዴ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የመንግስት መስረታ የተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ተደርገው ተሹመዋል፡፡
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልም ፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ተደርገው ተሰይመዋል፡፡
ከቀናት በፊት ደግሞ የመስኖና እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር የነበሩት አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኒኩለር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማ እና መሰረት ልማት ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ተደርገው ተሹመዋል፡፡

