● LivePolitics
የ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ የአገልግሎት ምዕራፍ ማጠቃለያ እና የቀጣይ ጉዞ ማስታወቂያ
A
By Ashenafi
Jul 8, 20261 min read
243
ባለፉት 5 ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበራቸው የሕዝብ ውክልና ትናንት በይፋ ማብቃቱን ተከትሎ የአገልግሎት ምዕራፍ ማጠቃለያ እና የቀጣይ ጉዞ ማስታወቂያ አጋርተዋል ::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ «አብረን እንስራ» በማለት ላቀረቡት ጥሪ እና በ7ኛው ዙር ምርጫ በባሕር ዳር ተወዳዳሪ ቢሆኑ ኖሮ እጩ ላለማቅረብ አስበው እንደነበርና በምክር ቤቱ ያነሷቸው ሐሳቦች ጠቃሚ እንደነበሩ ለገለጹላቸው አስተያየት እውቅና ሰጥተዋል።
ላለፉት 10 ዓመታት ከነበረው ድካም በኋላ፣ አሁን ራሳቸውን ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ (በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት) ያገለሉ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይ በሙያቸው ሀገርን ማገልገል፣ በግሉ ሴክተር (Startups) ላይ መሰማራት እና ለቤተሰብ ጊዜ መስጠት ላይ ያተኩራሉ። ቀጥተኛ ፖለቲካው ቢያበቃም የአማራን ሕዝብ አንድነትና አብሮነት በሚያጠናክሩ፣ የዜጎችን ኑሮ በሚያሻሽሉ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ለእውነተኛ ብሔራዊ ውይይት በሚረዱ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

